/ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።

ከኢብኑ ዓባስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ አንድ ጊዜ ዉዱእ አደርገዋል።"
ቡኻሪ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በአንድ አንድ ወቅቶች ዉዱእ ያደረጉ ጊዜ ሁሉንም የዉዱእ አካላቶቻቸው አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ያጥቡ ነበር። ፊታቸውን ‐ መጉመጥመጥና ውሀውን ወደ አፍንጫ ውስጥ ስቦ መልሶ ማውጣትን ጨምሮ‐ ፣ ሁለት እጃቸውንና ሁለት እግራቸውን አንድ አንድ ጊዜ ያጥቡ ነበር። ይህም ዝቅተኛው የግዴታ መጠን ነው።

Hadeeth benefits

  1. አካላቶቻችንን ስናጥብ ግዴታ ያለብን አንድ ጊዜ ብቻ ነው። ከዚህ በላይ መጨመር ተወዳጅ ነው።
  2. በአንድ አንድ ወቅቶች ላይ አንድ አንድ ጊዜ ብቻ ዉዱእ ማድረግ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ጭንቅላትን በማበስ ዙሪያ የተደነገገው አንድ ጊዜ ብቻ ማበስ ነው።