- በዉዱእ ወቅት ሁለት እግሮችን መታጠብ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን። (ከመታጠብ ይልቅ) ማበሱ ብቻ ቢፈቀድ ኖሮ ተረከዙን ማጠብ የተወን ሰው በእሳት አይዝቱበትም ነበርና።
- የሚታጠቡ አካላቶችን በትጥበት ማዳረስ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን። ማጠብ ግዴታ ከሆነበት አካል ሆነ ብሎም ይሁን ተዘናግቶ ትንሽ አካል ብትሆን እንኳ የተወ ሰው ሶላቱ ትክክለኛ አይሆንም።
- አላዋቂን ማስተማርና ማረም አንገብጋቢ መሆኑን እንረዳለን።
- ዐሊም (አዋቂ) የሆነ ሰው ግዴታዎችንም ይሁን ሱናዎችን ትተው ሲያይ ተገቢ በሆነ መልኩ ያወግዛል።
- ሙሐመድ ኢስሐቅ አድደህለዊ እንዲህ ብለዋል: ዉዱእን ማዳረስ ሶስት አይነት ነው። ግዴታ: ይህ የዉዱእን ቦታ አንድ ጊዜ ማዳረስ ነው። ሱና: ይህም ሶስት ጊዜ ማጠቡ ነው። ተወዳጅ: ይህም ሶስት ሶስት ጊዜ ከማጠብም ጋር ቦታዎቹን እያረዘመ መታጠብ ነው።