- በመልካም ለማዘዝ መፍጠን፣ መሃይማንንና ዝንጉዎችን ማንቃት በተለይ የሚሰራው ውግዝ ስራን ተከትሎ አምልኮ የሚበላሽበት ከሆነ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
- የዉዱእ አካላትን በውሃ ማዳረስ ግዴታ ነው። ከውዱእ አካላት ትንሽ እንኳ ብትሆን የተወሰነን የተወ ሰው ዉዱኡ ትክክል አይደለም። ዉዱእ ያደረገበት ወቅት ከረዘመ ደግሞ መድገም ግዴታው መሆኑን እንረዳለን።
- ዉዱኡን ማሳመር የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን። ይህም አሟልቶ በማድረግና በሸሪዓ በታዘዘው መልኩ በማዳረስ ነው።
- ሁለት እግሮች ከዉዱእ አካላት መሆናቸውን እንረዳለን። እነርሱን ማበስም በቂ አይደለም። የግድ መታጠብ አለባቸው።
- ሁሉንም የዉዱእ አካል ከበስተፊቱ ያለው ከመድረቁ በፊት በሚያጥብበት ልክ በዉዱእ አካላት መካከል ማከታተል ይገባል።
- አለማወቅና መርሳት ወንጀለኝነትን እንጂ ግዴታን አያነሱም። ዉዱኡን ያላዳረሰው ይህን ሰውዬ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ባለማወቁ ምክንያት እንዲደግመው አዘዙት እንጂ ውዱእ የማድረግ ግዴታውን አላነሱለትም።