- ዉዱእ የሌለው ሰው ከትልቁ ሐደሥ በትጥበት፤ ከትንሹ ሐደሥ ደግሞ በዉዱእ እስኪፀዳ ድረስ ሶላቱ ተቀባይነት አይኖረውም።
- ዉዱእ ማለት ውሀን አፍ ውስጥ በመያዝ አመላልሶ በመትፋት ከዚያም ውሀን ወደ አፍንጫ ውስጥ መሳብ ከዚያም ማውጣት፤ ቀጥሎ ፊቱን ሶስት ጊዜ ማጠብ፤ ቀጥሎ ሁለት እጆችን ክርንን ጨምሮ ሶስት ጊዜ ማጠብ፤ ቀጥሎ ጭንቅላትን ባጠቃላይ አንድ ጊዜ ማበስ፤ ቀጥሎ ሁለት እግሮችን ከቁርጭምጭሚቱ ጋር ሶስት ጊዜ ማጠብ ነው።