- በ "ላ ኢላሀ ኢለሏህ" የመመስከር ትርጉም አሏህን በአምልኮ መነጠልና ከአሏህ ውጭ ምንንም አለማምለክ እንደሆነ፤
- ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን የመመስከር ትርጉሙ በሳቸውም ማመን፣ ይዘውት በመጡትም እውነትነቱን ማመን፤ እሳቸው ወደ ሰው ልጆች ከተላኩት የመጨረሻው መልዕክተኛ መሆናቸውንም ማመን መሆኑን፤
- የእውቀት ባለቤት ወይም እርሱ ዘንድ ማምታቻ ያለውን ሰው ማናገር መሀይምን እንደማናገር አለመሆኑን፤ ስለዚህም ነው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሙዓዝን እንዲህ በማለት የጠቆሙት፡ "አንተ የመጽሐፍ ባለቤት ወደሆኑ ህዝቦች ትሄዳለህ።"
- ሙስሊም በዲኑ ጉዳይ አወዛጋቢዎች ከሚያመጡት ማምታቻ መጥራት እንዲችል በእውቀት ላይ ሊሆን እንደሚገባው፤ ይህም ዒልም በመፈለግ የሚሆን ነገር ነው።
- የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከተላኩ በኋላ የአይሁዶችና የክርስያኖች ሃይማኖት ውድቅ መሆኑን፤ በነቢያችን የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን አምነው ወደ እስልምና እስካልገቡ ድረስም ከሚድኑት ጎራ አለመሆናቸውን እንረዳለን።