- የተውሒድ ትሩፋት መገለፁ። እሱም አማኝ ሆኖ በአላህ ላይ አንዳችንም ሳያጋራ የሞተ ሰው ጀነት የሚገባ መሆኑን።
- የሺርክ አደገኝነትም መገለፁ። እሱም፥ በአላህ ላይ አንዳችን እያጋራ የሞተ ሰው እሳት የሚገባ መሆኑን።
- ከተውሒድ ሰዎች መካከል፥ ወንጀል የሰሩ በአላህ ፍላጎት እና ውሳኔ ስር መሆናቸው፤ በመሆኑም ከፈለገ እንደሚቀጣቸው ከፈለገም የሚምራቸው እንድሆነ እና ከዚያም መመለሻቸው ወደ ጀነት መሆኑን።