- "ላኢላሃ ኢለሏህ" ብሎ መናገርና ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ሁሉ መካድ ወደ ኢስላም ለመግባት መስፈርት ነው።
- የ "ላኢላሃ ኢለሏህ" ትርጉም በጣኦታት፣ በመቃብሮችና በሌሎችም ከአላህ ውጪ በሚመለኩ ሁሉ መካድና በአምልኮ እሱን ብቻ መነጠል ነው።
- ተውሒድን የተገበረና በውጫዊ ማንነቱ የአላህ ድንጋጌዎች ላይ የፀና ይህን የሚፃረር ነገር ከሱ ይፋ እስኪሆን ድረስ ከሱ መቆጠብ ግዴታ ነው።
- የሙስሊም ገንዘብ፣ ደሙና ክብሩ በሸሪዓዊ ምክንያቶች ካልሆነ በስተቀር የተከበረ መሆኑን እንረዳለን።
- በዱንያ ውስጥ ፍርድ የሚሰጠው በውጫዊ ማንነት ሲሆን በአኺራ ደግሞ ኒያዎችና አላማዎች ላይ በመንተራስ ነው።