- ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሙዓዝን ከመጓጓዣ እንስሳቸው ኋላ ማፈናጠጣቸው የሳቸውን መተናነስ ያስረዳናል።
- ሙዓዝ እሳቸው ለሚናገሩት ንግግር ንቃቱ እንዲበረታ ሙዓዝን ደጋግመው መጥራታቸው የነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለምን የማስተማር ስልት እንረዳለን።
- "ላኢላሃ ኢለሏህ እና ሙሐመድ ረሱሉሏህ" የሚሉት የምስክርነት ቃላት ካላቸው መስፈርቶች መካከል ተናጋሪው ሳይዋሽ ወይም ሳይጠራጠር እውነተኛና እርግጠኛ መሆኑ አንዱ ነው።
- የተውሒድ ሰዎች በጀሀነም እሳት ውስጥ አይዘወትሩም። በወንጀሎቻቸው አማካኝነት ቢገቡ እንኳ ከፀዱ በኋላ ከርሷ ይወጣሉ።
- ሁለቱ የምስክርነት ቃላቶችን በእውነት ለተናገረ ሰው ያላቸውን ትሩፋት እንረዳለን።
- ሐዲሥን በመናገር ተከትሎ የሚመጣ ችግር (መፍሰዳህ) ካለ አንዳንድ ጊዜ ሐዲሡን ከመናገር መቆጠብ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።