- አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገው ሐቅ መገለፁ፤ እሱም፥ ሊያመልኩትና በሱ ላይም ምንንም ላያጋሩ መሆኑ።
- አላህ በችሮታውና በፀጋው በነፍሱ ላይ ግዴታ ያደረገው የባሮች አላህ ዘንድ ያላቸው ሐቅ መገለፁ፤ እሱም ጀነት ሊያስገባቸውና ላይቀጣቸው ነው።
- እዚህ ሐዲሥ ውስጥ አላህ ላይ አንዳችንም የማያጋሩ የተውሒድ ሰዎች መመለሻቸው ጀነት መሆኑን የሚገልፅ ትልቅ ብስራት አለ።
- ሙዓዝ ዕውቀት በመደበቃቸው ወንጀል ውስጥ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ይህን ሐዲሥ የተናገሩት ከመሞታቸው በፊት (ወደ ሞት አፋፍ ሲቃረቡ) ነው።
- አንዳንድ ሐዲሦችን ከፊል ሰዎች ትርጉሙን በአግባቡ አይረዱትም ተብሎ ከተሰጋ አለመናገርን ያስገነዝበናል። ይህ የማንነግራቸው ግን በሐዲሡ ስር ተግባርን የሚያዝና ሸሪዐዊ የቅጣት ብይኖችን የሚያስቀምጥ ሐዲሥ ካልሆነ ነው።
- ከተውሒድ ሰዎች መካከል ወንጀል የሰሩ በአላህ ፍላጎት ስር መሆናቸው። ከፈለገ የሚቀጣቸው፤ ከፈለገም የሚምራቸው እነደሆነ እና መመለሻቸው ወደ ጀነት መሆኑን።