- ቤት በሚገቡበትና ምግብ በሚመገቡበት ወቅት አላህን ማውሳት እንደሚወደድ እንረዳለን። የቤቱ ባለቤቶች አላህን ካላወሱ ሰይጣን ቤቶች ውስጥም ያድራል፤ ከባለቤቶቹ ምግብም ይመገባል።
- ሰይጣን የሰውን ልጅ በስራው፣ በእንቅስቃሴውና በሁሉም ጉዳዩ ይጠባበቀዋል። ሰው ከዚክር (ከውዳሴ) በተዘናጋ ጊዜ ሸይጧንም ከርሱ የሚፈልገው ፍላጎቱን ያገኛል።
- ዚክር (ውዳሴ) ሰይጣንን እንደሚያባርር እንረዳለን።
- ሁሉም ሰይጣን በንግግሩ የሚደሰቱና ትእዛዙን የሚከተሉት ተከታይና ወዳጆች እንዳሉት እንረዳለን።