- ወደ መስጂድ በሚገባ ወቅትና ከመስጂድ በሚወጣ ወቅት ይህን ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
- ሲገባ እዝነትን በመጠየቅ ላይ ሲወጣ ደሞ ችሮታን በመጠየቅ ላይ የተገደበው: መስጂድ የሚገባ ሰው ወደ አላህና ወደ ጀነት በሚያቃርበው ነገሮች ላይ ነው የሚጠመደው ስለዚህ ከቦታው ጋር የሚስማማው እዝነትን መጠየቅ ነው። የወጣ ጊዜ ደሞ ከሲሳይ የአላህን ችሮታ ለመፈለግ በምድር ላይ ስለሚሯሯጥ ከቦታው ጋር የሚስማማው ችሮታ መወሳቱ ነው።
- እነዚህ ዚክሮች የሚባሉት መስጂድ መግባትና መውጣት ሲፈለግ እንደሆነ እንረዳለን።