- በአላህ መጠበቅ አምልኮ ነው። የተፈቀደ የሚሆነውም በአላህ ወይም በስሞቹና በባህሪያቶቹ ሲጠበቅ ነው።
- ከአላህ ባህሪያቶች መካከል አንዱ በሆነው የአላህ ቃል መጠበቅ እንደሚፈቀድ እንረዳለን። ይህም በማንኛውም ፍጡር ከመጠበቅ ተቃራኒ ሲሆን ከአላህ ውጪ ካለ አካል ጥበቃን መሻት ሺርክ ነው።
- የዚህ ዱዓእ ትሩፋትና በረከትን እንረዳለን።
- በዚክሮች መመሸግ (መከላከል) ሰው ከክፋቶች እንዲጠበቅ አንዱ ሰበብ ነው።
- በጋኔን ፣ በጠንቋይ፣ በአታላዮችና በሌሎችም ከአላህ ውጪ ባሉ አካላት ጥበቃ መፈለግ ውድቅ መደረጉ፤
- ይህ ዱዓእ በሀገሩም ይሁን በጉዞ አንድ ስፍራ ላይ ላረፈ ሰው መደንገጉን እንረዳለን።