/ በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'

በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'

ጃቢር ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለቱ ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፡ "በላጩ ዚክር 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ' ማለት ሲሆን በላጩ ዱዓእ ደግሞ 'አልሐምዱሊላህ' ማለት ነው።'"
ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ ውስጥ፣ ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በላጩ ዚክር "ላ ኢላሃ ኢለሏህ" - ትርጉሙም፡ ከአሏህ በቀር በእውነት አምልኮ የሚገባው የለም - መሆኑን፤ ከዱዓእ በላጩ ደግሞ "አልሐምዱሊላህ" - ትርጉሙም፡ ፀጋንም የሚውለው ለተሟላ ውብ መገለጫም የተገባው እርሱ አላህ ብቻ መሆኑን ማመን - እንደሆነ ተናገሩ።

Hadeeth benefits

  1. አሏህን በተውሒድ ቃል ማስታወስና በምስጋና ቃል መማፀን ማብዛት መበረታታቱን እንረዳለን።