/ ''ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ ወላኢላሃ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር' ማለቴ ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ (ከሚሰጠኝ) የበለጠ ወደእኔ እጅግ ተወዳጅ ነው።'

''ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ ወላኢላሃ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር' ማለቴ ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ (ከሚሰጠኝ) የበለጠ ወደእኔ እጅግ ተወዳጅ ነው።'

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብሏል: "የአላህ መልዕክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወስለም እንዲህ ብለዋል፡ ''ሱብሓነሏህ ወልሐምዱሊላህ ወላኢላሃ ኢለሏህ ወሏሁ አክበር' ማለቴ ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ (ከሚሰጠኝ) የበለጠ ወደእኔ እጅግ ተወዳጅ ነው።'"
ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ትላልቅ ቃላቶች አላህን ማወደስ ከዱንያና በውስጧ ካለው ሁሉ የተሻለ መሆኑን ተናገሩ። እነሱም: "ሱብሓነሏህ" ይህም አላህን ከጉድለት ማጥራት ነው። "አልሐምዱሊላህ" ይህም አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕ ባህሪያቶቹ ማወደስ ነው። "ላኢላሃ ኢለሏህ" ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም። "አሏሁ አክበር" አላህ ከሁሉም ነገር የበለጠ ታላቅ ነው ማለት ነው።

Hadeeth benefits

  1. አላህን በማውሳት ላይ መነሳሳቱ። አላህን ማውሳት ፀሀይ የወጣችበት ክልል ሁሉ ከሚሰጠን የበለጠ ተወዳጅ ነውና።
  2. ውዳሴ ማብዛት ደረጃና ምንዳ ስላለው በርሱ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  3. የዱንያ መጣቀሚያ ትንሽ ነው። ስሜትን የሚያስደስቱ ነገሮቿ ጠፊ ናቸው።