- ንፅህና ሁለት አይነት ነው። ውጫዊ ንፅህና በዉዱእ እና በገላ ትጥበት ሲሆን፤ ውስጣዊ ንፅህና ደግሞ በተውሒድ፣ በኢማንና መልካም ስራ የሚመጣ ነው።
- ሰላት ለአንድ ባሪያ በዱንያም ሆነ በትንሳኤ ቀን ብርሃን ስለሆነ ሰላትን በጥንቃቄ መስገድ አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
- ምፅዋት የእውነተኛ ኢማን ማስረጃ ነው።
- ቁርኣን በአንተ ላይ ሳይሆን ለአንተ ማስረጃ እንዲሆን ቁርኣንን መተግበር እና ማመን አንገብጋቢ ጉዳይ መሆኑን እንረዳለን።
- ነፍስ በአምልኮ ካልጠመድካት በወንጀል ታጠምድሀለች።
- ሁሉም ሰው መስራቱ የማይቀር ጉዳይ ነው። ወይ ነፍሱን በአምልኮ ነፃ ያወጣታል ወይም በወንጀል ለጥፋት ይዳርጋታል።
- ትዕግስት እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ ቻይነትንና ምንዳን ከአላህ ማሰብ ይፈልጋል።