- የነቢዩን (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሐዲሥ በመሸምደድና ለሰዎች በማድረስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- የሐዲሥ ምሁራኖች ያላቸው ደረጃና ሐዲሥን የመፈለግ ልቅና መገለፁ፤
- የግንዛቤ ባለቤቶች የሆኑት ዑለማዎች ያላቸው ደረጃን እንረዳለን።
- ሶሐቦች (ሪድዋኑሏሁ ዐለይሂም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሐዲሥን ሰምተው ለኛ ማድረሳቸው የነርሱን ደረጃ ያስረዳናል።
- አልመናዊ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ ሐዲሥን ለማስተላለፍ ሐዲሡን ፈቂህ (መገንዘብ) መስፈርት እንዳልሆነ ገለፆልናል። ሐዲሥ ለማስተላለፍ መስፈርቱ መሸምደድ ነው። ፈቂህ (በደንብ ተገንዛቢ) የሆነ ሰው ደግሞ ሐዲሡን መገንዘብና ማስተንተን ይገባዋል።"
- ኢብኑ ዑየይናህ እንዲህ ብለዋል: "ሐዲሥን የሚፈልግ ሰው ሁሉ በዚህ ሐዲሥ መሰረት ፊቱ ላይ ብርሃን አለው።"
- የሐዲሥ ሊቃውንቶች ዘንድ ሽምደዳ ሁለት አይነት ነው: እነርሱም: በቀልብ መሸምደድ እና በመጽሐፍና በጽሑፍ መጠበቅ ነው። ሁለቱንም ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው ዱዓእ ይጠቀልላቸዋል።
- የሰዎች ግንዛቤ ይበላለጣል። አንዳንድ ሐዲሥ የደረሳቸው መጀመርያ ከሰማው የበለጠ ተገንዛቢ ሊሆኑ ይችላሉ፤ ፊቂህን የተሸከሙ ሆነው (ፈቂህ ያልሆኑ) ግንዛቤ የሌላቸውም ስንትና ስንት ሰዎች ይኖራሉ?!