- ሸሪዐዊ ዕውቀት እና እርሱን መማር ያለው ትሩፋት ትልቅ መሆኑንና በርሱም ላይ መነሳሳቱን ተረድተናል፤
- በእዚህ ኡማህ ውስጥ በእውነት ላይ የሚቆም መኖሩ የማይቀር ጉዳይ መሆኑን፤ ከእውነተኛ መንገድ አንዱ ሲገለል ሌላው በእውነት ላይ ይቆማል።
- ሃይማኖትን መገንዘብ አላህ ለባሪያው መልካም ከመሻቱ የሚመደብ መሆኑን ፤
- ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚሰጡት በአላህ ትእዛዝና ፍላጎት ብቻ መሆኑንና ያለርሱ ፈቃድ አንድም ነገር ማድረግ እንደማይችሉ ተረድተናል።