- ሃይማኖቱን በአግባቡ ከመተግበር የሚከለክሉ ግርዶሾች ከመምጣታቸው በፊት ሃይማኖትን አጥብቆ መያዝና ወደ መልካም ስራ መቻኮል ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
- በመጨረሻው ዘመን አጥማሚ ፈተናዎች ተከታትለው እንደሚመጡ መጠቆማቸው። ይህም አንድ ፈተና በተወገደች ቁጥር ሌላ ፈተና ይከተላታል።
- የሰው ልጅ እምነት በደከመ ጊዜና ለገንዘብም ሆነ ለሌላ ዓለማዊ ጉዳዮች እምነቱን አሳልፎ ከሰጠ ይህ ከእምነቱ ለመጣመም፣ እምነቱን ለመተዉና ከፈተና ጋር አብሮ ለመነዳቱ ሰበብ ይሆንበታል።
- እዚህ ሐዲሥ ውስጥ መልካም ስራዎች ከፈተና ለመዳን ምክንያት እንደሆኑ ይጠቁማል።
- ፈተናዎች በሁለት ይከፈላሉ:- አንዱ የማምታቻ (የሹበሃ) ፈተናዎች ሲሆን መፍትሄውም ዕውቀት ነው። ሌላው ደግሞ የዝንባሌ/ ፍላጎት (የሸህዋ) ፈተናዎች ሲሆን መፍትሄውም ኢማንና ትእግስት ነው።
- ይህ ሐዲሥ ስራው ያነሰ ሰው ፈተና ወደርሱ በፍጥነት እንደሚመጣና ስራው የበዛ ሰው ደግሞ በሰራው ስራ (ተመፃድቆ) መሸወድ እንደማይገባውና ይልቁንም ጨምሮ ማብዛት እንዳለበት ይጠቁማል።