/ አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።

አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።

አቢ ሙሳ አል-አሽዓሪይ ረዲየሏሁ ዐንሁ እንዲህ ማለታቸው ተላልፏል፡ "የአሏህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፡ "አንድ ሰው በታመመ ወይም ጉዞ በወጣ ወቅት ሀገሩ እያለና ጤናማ ሳለ እንደሚያደርገው አጅር ይጻፍለታል።"
ቡኻሪ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ስለአሏህ እዝነትና ችሮታ እየነገሩን ነው። ይህም አንድ ሙስሊም በሀገሩ እና ጤነኛ ሳለ ልምድ ያደረገው መልካም ስራ ከዚያም ዑዝር ገጥሞት ታሞ ማድረግ ባይችል፣ ወይም በጉዞ ወይም ደግሞ በሌላ በየትኛውም ትክክለኛ ምክንያት ሳያደርገው ቢቀር ልክ ጤነኛና በሀገሩ ሆኖ ሲያደርግ እንደነበረው ምንዳ ሙሉ ሆኖ ይጻፍለታል።

Hadeeth benefits

  1. አሏህ በባሮቹ ላይ ያለው ችሮታ ስፋቱ፤
  2. ጤነኛ በሆንን እና ትርፍ ጊዜ ባገኘንበት አጋጣሚ መልካም ተግባርና ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም መበርታት እንደሚገባን እንረዳለን።