- በደስታ ወቅት ማመስገንና በጉዳት ወቅት መታገስ ያለውን ትሩፋት እንረዳለን። ይህንን የፈፀመም በሁለቱም ሀገሮች መልካምን ያገኛል። በፀጋዎች ላይ ያላመሰገነና በመከራዎች ላይ ያልታገሰ ሰው ምንዳም ያመልጠዋል ወንጀልም ይኖርበታል።
- የኢማንን ደረጃ እንረዳለን። በየትኛውም ሁኔታ ምንዳ ማግኘት ለኢማን ባለቤቶች ካልሆነ በቀር ለማንም አይሆንም።
- በደስታ ወቅት ማመስገንና በጉዳት ወቅት መታገስ ከአማኞች መገለጫ መካከል አንዱ እንደሆነ እንረዳለን።
- በአላህ ውሳኔና ፍርድ ማመን አማኝን በሁሉም ሁኔታዎቹ ላይ የተሟላ ውዴታ እንዲኖረው ያደርገዋል። ይህም ከአማኝ ውጪ ካለ ሰው በተቃራኒው ነው። አማኝ ያልሆነ ሰው ጉዳት በሚያጋጥመው ወቅት ዘውታሪ ብስጭት ላይ ይሆናል። ከአላህ የሆኑ ፀጋዎች ባገኘ ወቅትም በፀጋው አላህን በሚወደው ላይ ቀርቶ ጭራሽ አሏህን ለማመፅ ይጠቀምበታል።