- አላህ ለአማኝ ባሮቹ ካለው እዝነት በዱንያ መከራዎችና ፈተናዎች አማካይነት በዱንያ ላይ እያሉ ወንጀሎቻቸውን ከነርሱ መማሩ ነው።
- መከራ ብቻውን ወንጀልን ያስምራል ለዚህም አምኖ መገኘት ቅድመ መስፈርቱ ነው። አንድ ባሪያ ከታገሰና ካልተማረረ ይመነዳል።
- በሚወደውም፣ በሚጠላውም በሁሉም ጉዳዮች በመታገስ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። የአላህን ምንዳ በመፈለግና ቅጣቱን በመፍራት አላህ ግዴታ ያደረገበትን በአግባቡ በመፈፀምና አላህ ክልክል ያደረገበትን ነገር በመራቅ ላይ መታገስ ይገባዋል።
- ሐዲሡ ውስጥ "በአማኝ ወንድና ሴት ላይ" የሚለው ንግግር: አማኝ ሴት የሚለው መጨመሩ ለሴቶች ተጨማሪ አፅንዖት ለመስጠት ነው። ያለበለዚያ "አማኝ" ብቻ ቢሉም በዚህ ውስጥ ሴት ትጠቃለል ነበር። ጉዳዩ በወንድ ላይ ብቻ የተገደበ አይደለምና። መከራ በሴት ላይም ቢከሰት ልክ እንደወንዱ ወንጀሏና ኃጢአቷ በመማር ተመሳሳይ ምንዳ ቃል ተገብቶላታል።**
- አንድ ባሪያ በተደጋጋሚ በሚያጋጥሙት ህመሞች ላይ ከሚያቀሉለት ነገሮች አንዱ መከራውን ተከትለው የሚያገኛቸው ትሩፋቶች ናቸው።