- ነጭ ሽንኩርት ወይም ቀይ ሽንኩርት ወይም ባሮ የበላ ሰው መስጂድ ከመምጣት መከልከሉን እንረዳለን።
- እንደ ሲጃራ ጭስ፣ ትምባሆና የመሳሰሉት ሰጋጆች የሚታወኩበት መጥፎ ሽታ ያለው ሁሉ በፍርድ ወደነዚህ ነገሮች ይጠጋሉ።
- የመከልከሉ ምክንያት ሽታ ነው። ስለዚህ አብዝቶ በመቀቀል ወይም በሌላ መንገድ ሽታው ቢወገድ መጠላቱም አብሮ ይወገዳል።
- መስጂድ ውስጥ የጀመዓ ሶላት ስለሚያስመልጠው መስጂድ ውስጥ ጀመዓ ሶላት መስገድ ባለበት ሰው ላይ እነዚህ ነገሮችን መብላቱ ይጠላል። መስጂድ የመገኘት ግዴታው እንዲነሳለት ብሎ ለዘዴ መብላቱ ግን ይከለከላል።
- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ነጭ ሽንኩርትና የመሳሰሉትን ከመብላት የተቆጠቡት ክልክል ስለሆነ ሳይሆን ጂብሪልን (ዐለይሂ ሰላም) ስለሚያወሩ ነው።
- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ብይንን ከምክንያቱ ጋር አቆራኝተው መናገራቸው የርሳቸውን የማስተማር ውበት ያሳየናል። ይህም የሚያናግሩት ሰው የመከልከል ጥበቡን በማወቅ ልቡ እንዲረጋጋ ነው።
- ቃዲ እንዲህ ብለዋል: «ዑለማዎች ይህን ሐዲሥ በመመርኮዝ ከመስጂድ ውጪ ያሉ የሶላት መሰብሰቢያዎችን እንደ ዒድና ጀናዛ ሶላት ለመስገድ የሚሰበሰቡበትን አይነቱ፣ የአምልኮ መሰብሰቢያ፣ ልክ እንደዚሁ የእውቀት፣ የዚክር፣ የሰርግ ድግስና የመሳሰሉት መሰብሰቢያዎችን መስጂድ ውስጥ ከሚሰገዱት ጋር በዚሁ ፍርድ አመሳስለዋቸዋል። ሱቅና የመሳሰሉት ግን የዚህ ሐዲሥ መልእክት ውስጥ አይገቡም።»
- ዑለማዎች እንዲህ ብለዋል: እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ነጭ ሽንኩርትና የመሳሰሉትን የበላ ሰው መስጂዱ ባዶ እንኳ ቢሆን መስጂድ ውስጥ ከመግባት መከልከሉን ይጠቁመናል። ይህም መላእክቶች የሚኖሩበት ስለሆነና የሐዲሡ ጥቅል ሀሳብ ይህንን ስለሚጠቁም ነው።