- የነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ስነ ምግባር ማማር፤ ከባልደረቦቻቸው ጋር የሚቀመጡ መሆናቸውን እነሱም ከሳቸው ጋር እንደሚቀመጡ ፤
- ለጠያቂ ገር መሆንና ማቅረብ የተደነገገ መሆኑን፤ ይህም ሳይጨናነቅና ሳይፈራ ለመጠየቅ እንዲመቻች ነው።
- ልክ ጂብሪል እውቀት ሊቀስም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፊት ስርአት ያለውን አቀማመጥ በመቀመጥ እንደተገበረ ከአስተማሪ ጋር አደብ መያዝ እንደሚገባ ፤
- የኢስላም ማዕዘናት አምስት የኢማን መሰረቶች ደግሞ ስድስት መሆናቸውን፤
- "ኢስላም" የሚለው ቃልና "ኢማን" የሚለው ቃል አንድ ላይ ሲመጡ "ኢስላም" ውጫዊ በሆኑ ነገሮች ሲተረጎም "ኢማን" ደግሞ ውስጣዊ በሆኑ ነገሮች ይተረጎማል።
- የኢስላም ሃይማኖት የሚበላለጡ ደረጃዎች እንዳሉት መገለፁ፤ የመጀመሪያው ደረጃ: ኢስላም ፣ ሁለተኛው: ኢማን ፣ ሶስተኛው: ኢሕሳን ነው። እርሱ (ኢሕሳን) ከፍተኛው ደረጃ ነው።
- የጠያቂ መሰረቱ አለማወቅ ነው። አለማወቅ ነው ለጥያቄ የሚያነሳሳው። ለዚህም ነው ሶሐቦች እየጠየቀም የመልሱን እውነተኝነት ሲያረጋግጥ የተደነቁት።
- እጅግ አንገብጋቢ ከሆነ ነጥብ መጀመር እንደሚገባ፤ እሳቸው ኢስላምን ሲያብራሩ በሁለቱ የምስክርነት ቃላት ነውና የጀመሩት፣ ኢማንን ሲያብራሩም በአላህ ከማመን ነውና የጀመሩት፤
- ጠያቂው የሚያውቀውን ነገር ሌሎችን ለማሳወቅ ሲል የእውቀት ባለቤቶችን መጠየቅ እንደሚችል፤
- የሰዓቲቱ እለት እውቀት አላህ በእውቀቱ ከተነጠለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው።