- ሴቶች ወደ ዒድ ሶላት መውጣታቸውና ለብቻቸው መመከራቸው እንደሚወደድ እንረዳለን።
- አኗኗሪን መካድና እርግማን ማብዛት ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል ነው። የእሳት ዛቻ መምጣቱ ወንጀሉ ትልቅ የመሆኑ ምልክት ነውና።
- እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ኢማን እንደሚጨምርና እንደሚቀንስ ተገልጿል። አምልኮው የበዛ ሰው ኢማኑና ዲኑ ይጨምራል። አምልኮው የጎደለችበት ሰው ደግሞ ዲኑም ይጎላል።
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «አይምሮ መጨመርና መቀነስን የሚቀበል ነው። ኢማንም ልክ እንደዛው። ሴቶች ማጓደላቸው ከተፈጥሮ የመጣ ስለሆነ ይህ መጠቀሱ እነርሱን መውቀስ ተፈልጎበት አይደለም። ነገር ግን በዚህ ማንቃት የፈለጉት በነርሱ ከመፈተን ማስጠንቀቅን ነው። ስለዚህም እንደሚቀጡበት የተናገሩት አኗኗሪን በመካዳቸውና በሌሎቹ እንጂ በተፈጥሯዊ ጉድለታቸው አይደለም። የዲን ጉድለት መከሰቱ ወንጀል በመፈፀም ብቻ የታጠረ ሳይሆን ከዛም የሰፋ እንደሆነ እንረዳለን።
- ይህ ሐዲሥ ተማሪ የሆነ ሰው አዋቂን፣ ተከታይ የሆነ ሰው መሪውን የተናገሩት ንግግር ሀሳቡ ግልፅ ካልሆነላቸው ድጋሚ ማብራሪያ መጠየቅ እንደሚፈቀድ ያስረዳናል።
- ይህ ሐዲሥ የሴት ልጅ ምስክርነት የወንድን ልጅ ምስክርነት ግማሽ እንደሆነ ያስረዳናል። ይህም ቃሏን ጠብቃ ማቅረብ ላይ ጉድለት ስላለባት ነው።
- ኢብኑ ሐጀር "አይምሯቸው የጎደለ አልተመለከትኩም ...." በሚለው ነቢያዊ ንግግር ዙሪያ እንዲህ ብለዋል: "ለኔ በግልፅ የሚታየኝ እንዲህ መሆናቸው በራሱ አብዛኛው የእሳት ነዋሪ እንዲሆኑ ያደረጋቸው አንዱ ምክንያት ነው። ተገቢ ያልሆነን ነገር እንዲሰራ ወይም እንዲናገር እነርሱ የቆራጥ ወንድን ልጅ አይምሮ ለመውሰድ ምክንያት በመሆን አስተዋፅኦ ካበረከቱ በወንጀሉ ላይ በርግጥም ተባብረዋልና ከወንዶችም በላይ እሳት ውስጥ ይበዛሉ።"
- ሴት ልጅ በወር አበባዋ ጊዜ ከሶላትና ጾም መከልከሏን እንረዳለን። በወሊድ ደም ጊዜዋም ተመሳሳይ ነው። ከዚያም በፀዱበት ጊዜ ፆምን ብቻ ቀዿ ያወጣሉ።
- ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከሴቶች የመጡ ጥያቄዎችን ያለምንም ማጥላላትና ወቀሳ መመለሳቸው የርሳቸው ስነምግባር ያማረ መሆኑን ያስረዳናል።
- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ሶደቃ ቅጣትን ይከላከላል። በፍጡራን መካከል የሚሰራን ወንጀልም ያስምራል።"
- ነወዊ እንዲህ ብለዋል: "የሴቶች ዲን የመቀነሱ ምክንያት በወር አበባ ወቅት ሶላትና ጾምን በመተዋቸው ምክንያት ነው። አምልኮ ያበዛ ሰው ኢማኑና ዲኑም ይጨምራልና። አምልኮው የቀነሰ ሰው ዲኑም ይቀንሳል። ከዚያም የዲን መቀነስ ወንጀለኛ በሚኮንበት መልኩ ሊሆንም ይችላል። ይህም ያለ በቂ ምክንያት ሶላትን ወይም ጾምን ወይም ከነርሱ ውጪ ያሉንም ግዴታ አምልኮዎችን እንደተወ ሰው አይነቱ ነው። ወንጀለኛ በማይኮንበት መልኩ ሊሆንም ይችላል። ጁሙዓን ወይም ጂሃድን ወይም ከዚህ ውጪ ያሉ ግዴታ ያልሆኑበትን ነገሮች ያለ በቂ ምክንያት እንደተወ ሰው አይነቱ ነው። እንዲተው በሸሪዓ የተገደደበትን ነገር በመተው መልኩም ሊሆን ይችላል። የወር አበባ ላይ ያለች ሴት ሶላትና ጾምን መተዋን ይመስል።"