- ሶሐቦች ለሌሎች መፈፀም ያለባቸውን ሐቅና ለነርሱ ያላቸውን ሐቅ ለማወቅ የሚያደርጉትን ጥረት እንረዳለን።
- አንድ ባል ለሚስቱ ቀለብ፣ ልብስና መኖሪያ ቤት ማሟላቱ ግዴታው እንደሆነ እንረዳለን።
- ውስጣዊም ሆነ ውጫዊ ማጥላላት እንደሚከለከል እንረዳለን።
- ከተከለከሉት ማጥላላቶች መካከል: አንቺ ከወራዳ ጎሳ የመጣሽ ነሽ ወይም ከመጥፎ ቤተሰብ የተገኘሽ ነሽ ወይም ይህን የመሳሰሉ ንግግሮች መናገር አንዱ ነው።