- ጥንቁቅነትን አጥብቆ በመያዝ ላይና በዱንያ ውጫዊ ገፅታና ጌጧ አለመሸወድ ላይ መነሳሳቱ።
- ሴቶችን በማየት ወይም ከባዕድ ወንዶች ጋር መቀላቀላቸውን በማቃለል ወይም ከዚህ ውጪም ባሉ መፈተኛዎች በሴቶች ፈተና ከመውደቅ መጠንቀቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
- የሴቶች ፈተና ከዱንያ እጅግ ትላልቅ ፈተናዎች መካከል አንዱ ነው።
- ባለፉት ህዝቦች መገሰፅና ትምህርትን መውሰድ እንደሚገባ እንረዳለን። በኒ ኢስራኢሎች ላይ የተከሰተው ሌላውም ላይ ሊከሰት ይችላልና።
- የሴቶች ፈተና ሲባል ሚስት ከሆነች ሰውየውን ከአቅሙ በላይ በሆነ ወጪ ታስገድደውና በዚህም ዲናዊ ጉዳዮችን ከመፈለግ ጠምዳው ሙሉ ጊዜውን ዱንያን በመፈለግ ላይ እያዋለ እንዲጠፋ ታደርገዋለች፤ ባዕድ ሴት ከሆነች ደግሞ የርሷ ፈተና ከቤቷ በምትወጣ ወቅትና ከወንዶች ጋር በምትቀላቀል ጊዜ ወንዶችን ማታለሏና ከእውነት ዞር እንዲሉ ማድረጓ ነው። በተለይ ደግሞ የተራቆቱና የተገላለጡ ከሆኑ እንደየደረጃው ዝሙት ላይ ወደ ለመውደቅ ይዳርጓቸዋል። ስለዚህም የትኛውም አማኝ በአላህ ለመጠበቅና ከነርሱ ፈተና ለመዳን ከአላህ ጋር ትስስሩን ማጠንከር ይገባዋል።