- ሴት ልጅ ያለ ቅርብ ዘመዷ መጓዟ አለመፈቀዱን እንረዳለን።
- ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) "ባሏ ወይም ቅርብ ዘመዷ" ስላሉ፤ ሴት ልጅ ለሴት ልጅ ጉዞ ላይ መሕረም አትሆንም።
- ጉዞ ተብሎ የሚጠራን ሁሉ ሴት ልጅ ከባሏ ጋር ወይም ቅርብ ዘመዷ ጋር ካልሆነች በቀር መጓዟ ትከለከላለች። በዚህ ሐዲሥ የተጠቀሰውም ከጠያቂውና ከስፍራው መጠን አንፃር ነው።
- የሴት ልጅ መሕረም የሚባለው ባሏ ወይም እንደ አባት፣ ልጅ፣ አጎት የመሰሉ በቅርብ ዝምድና ምክንያት ከነርሱ ጋር መጋባትን ለዘላልም እርም የተደረገባት አካላቶች፤ ወይም እንደጥቢ አባቷ፣ የጥቢ አጎቷ ይመስል በጥቢ ምክንያት ከነርሱ ጋር ለዘላለም መጋባትን እርም የተደረገባት አካላቶች፤ ወይም እንደባል አባት የመሰሉ በአማችነት ምክንያት ከነርሱ ጋር መጋባትን እርም የተደረገባት አካላት ናቸው። "መሕረም" የተባለው ሙስሊም፣ አቅመ አዳም የደረሰ፣ ጤነኛና ታማኝ መሆን ይገባዋል። ከመሕረሙ የተፈለገው ነገር ሴትን መጠበቅ ከለላ መሆንና የሚያስፈልጋትን ማሟላት ነውና።
- ኢስላማዊ ሸሪዓ በሴት ጉዳይ ትኩረት መስጠቱን፣ መጠበቁንና ከለላ መሆኑን እንረዳለን።
- ልቅ የሆኑ (በጊዜ ያልተገደቡ) ሱና ሶላቶች ከፈጅርና ዐስር ሶላት በኋላ ተቀባይነት እንደሌላቸው እንረዳለን። ከዚህ ውስጥ ግን ያመለጡ ግዴታ ሶላቶችና እንደተሒየተል መስጂድ ያሉት ምክንያት ያላቸው ሶላቶች ተለይተው ይወጣሉ።
- ፀሀይ ከወጣች በኋላ በቀጥታ ሶላት መስገድ ክልክል ነው። ይልቁንም የግድ ከአስር ደቂቃ እስከ ሩብ ሰአት ያክል ቆይቶ የጦር ርዝመት ያክል ከፍ እስክትል ድረስ መጠበቅ ይገባል።
- የዐስር ወቅት ፀሀይ እስክትገባ ድረስ ይረዝማል።
- ከዚህ ሐዲሥ ወደ ሶስቱ መስጊድ ጓዝ ሸክፈን መጓዝ እንደሚፈቀድ እንረዳለን።
- የሶስቱ መስጂዶችን ትሩፋትና ከሌሎች መስጂዶች የተለዩ መሆናቸውን እንረዳለን።
- የነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ቀብር እንኳ ቢሆን ቀብሮችን ለመዘየር መጓዝ እንደማይፈቀድ እንረዳለን። መዲና ውስጥ ላለ ወይም ለሸሪዓዊና ለተፈቀደ ዓላማ ለመጣ ሰው ግን መዘየሩ ይፈቀድለታል።