/ ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።

ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ: "ሟቾችን አትሳደቡ! እነርሱ ወዳስቀደሙት (ስራቸው) ሂደዋልና።"
ቡኻሪ ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሟቾችን መሳደብና ክብራቸውን መንካት ክልክል መሆኑን አብራሩ። ከእኩይ ስነ ምግባሮችም የሚመደብ እንደሆነ ገለፁ። ምክንያቱም ይህ ስድብ በህይወት ያሉ ሰዎችን ከመጉዳት የዘለለ ለነርሱ የማይደርሳቸው ከመሆኑም በተጨማሪ እነሱ ወዳስቀደሙት መልካምም ይሁን መጥፎ ስራቸው ደርሰዋልና።

Hadeeth benefits

  1. ሐዱሡ ሟቾችን መሳደብ ክልክል መሆኑን ይጠቁማል።
  2. ሟቾችን ከመሳደብ መታቀብ የህያው ሰዎችን ጥቅምም የማህበረሰቡንም ሰላም ከመጣላትና ከመናቆር ይጠብቃል።
  3. ሟቾችን ከመሳደብ የመከልከሉ ጥበብ ወዳስቀደሙት ስራ ስለደረሱ መስደቡ ከንቱ ስለሆነና በተጨማሪ የህያው ቅርብ ዘመዶቹን ስለሚያውክ ነው።
  4. የሰው ልጅ ጥቅም የሌለውን ነገር መናገር አይገባውም።