- ወንጀል ለመስራት በልቡ የቆረጠና መዳረሻዎቹን የፈፀመ ሰው ለቅጣት የተገባ መሆኑን፤
- ሙስሊሞች እርስ በርስ በመጋደላቸው ዙሪያ ብርቱ ማስጠንቀቂያና የእሳት ዛቻም መምጣቱን፤
- በሙስሊሞች መካከል የተፈጠረው መጋደል በእውነት ጉዳይ ከሆነ ዛቻ ውስጥ አይካተትም። ለምሳሌ ከመሪ ትእዛዝ የወጡ ወሰን አላፊዎችና ሀገር የሚያበላሹን መዋጋትን ይመስል።
- ከባድ ወንጀል የሰራ ሰው በመስራቱ ብቻ ከሀዲ አይሆንም። ምክንያቱም ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁለቱን እርስ በርስ የሚጋደሉትን ሙስሊሞች ብለው ጠርተዋቸዋልና።
- ሁለት ሙስሊሞች በማንኛውም ለመግደል የሚያደርስ በሆነ መሳሪያ ሊጋደሉ ተገናኝተው አንዱ አንዱን ቢገድል ገዳዩም ተገዳዩም እሳት ውስጥ ናቸው። ሐዲሡ ውስጥ ሰይፍ መጠቀሱ ለምሳሌ ያክል ብቻ ነው።