- የዒደል ፊጥርና አድሓ ቀናትን መጾም ክልክል ነው። እንዲሁም የአያመ ተሽሪቅ ቀናትም ዒደል አድሓን ተከትለው የሚመጡ ቀናት ስለሆኑ ሐጅ ላይ ሆኖ የሚያርደውን ያላገኘ ሰው እስካልሆነ ድረስ መጾም ክልክል ነው። ሐጅ ላይ የሚያርደው ያጣ ግን ለርሱ አያመ ተሽሪቆችን መጾም ይፈቀድለታል።
- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: «ሁለቱ ቀናት ባህሪያቸውን ገልፆ የመከልከሉ አስፈላጊነት ማፍጠር ግዴታ የሆነበትን ምክንያት ለመጠቆም ነው ተብሏል። እርሱም በዒደል ፊጥር ከጾም መለያየታችንንና ከዚህ ቀን በኋላ ያለውን ቀን በመብላት ጾሙ መሙላቱን ለማሳየት ሲሆን ዒደል አድሓ ደግሞ በማረድ ቁርባን ያቀረበ ሰው ካረደው እንዲበላ ነው።»
- ኹጥባ አድራጊ ሰው በኹጥባው ወቅት ከጊዜው ጋር ተያያዥ የሆኑን ህግጋት ማውሳትና አጋጣሚዎችን ማጥናቱ ይወደድለታል።
- ከኡዱሒያ እርድ መብላት በሸሪዓ የተደነገገ መሆኑን እንረዳለን።