- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: «በአላህ መንገድ ላይ ሆኖ መጾም የሚያስገኘው ትሩፋት የሚተረጎመው በመጾሙ የማይጎዳ ለሆነ፤ በመጾሙ የሌሎችን ሐቆች የማያስመልጥ ለሆነ፤ የመዋጋቱና ሌሎች የጦርነት ግዳጆቹ ላይ የማያጓድል ለሆነ ሰው ነው።»
- ሱና ጾም በመጾም ላይ መነሳሳቱንና መበረታታቱን እንረዳለን።
- ሥራን ለአላህ ማጥራትና በርሱ የአላህን ውዴታ መፈለግ ግዴታ ነው። ለይዩልኝ፣ ለይስሙልኝና ለሌሎች አላማ ብሎ መጾም የለበትም።
- ሲንዲይ እንዲህ ብለዋል: «ሐዲሡ ውስጥ (በአላህ መንገድ) የሚለው ኒያን ማስተካከል ብቻ (ለአላህ ብሎ) በማለትም ሊተረጎም ይችላል፤ ዘመቻ ላይ ሆኖ የጾመ በማለት ሊተረጎምም ይችላል። ወደ አዕምሮ ፈጥኖ የሚገባው ሀሳብ ግን ሁለተኛው ትርጉም ነው።»
- ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: ሐዲሡ ውስጥ (ሰባ መኸር) የሚለው ንግግር: መኸር ከዓመቱ ወቅቶች ውስጥ የሚታወቅ ጊዜ ያለው ወቅት ነው። ሐዲሡ ውስጥ የተፈለገው ግን ዓመትን ለመግለፅ ነው። ሌሎችን የዓመቱ ክፍለጊዜያት (በጋ፣ክረምት፣ በልግን) ትተው መኸርን ለይተው የጠቀሱት መኸር ዘር የሚቀጠፍበት ምርጡ ክፍለጊዜ ስለሆነ ነው።