- በላጭ የሆኑ ወቅቶችን በመልካም ስራ ላይ ሆነን እንድናሳልፍ መነሳሳቱን እንረዳለን።
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሐዲሥ በረመዷን የመጨረሻ አስሩ ቀናቶች አምልኮ መጨመርና ሌሊቱንም በአምልኮ ህያው ሆኖ ማሳለፍ እንደሚወደድ ያስረዳናል።"
- አንድ ባሪያ ቤተሰቦቹን ወደ አምልኮ በማዘዝ ላይ ጥረት ሊያደርግና በዛም ላይ ሊታገስ ይገባዋል።
- መልካም ተግባራትን መስራት ቆራጥነትን፣ ትግስትንና መበረታታትን ይፈልጋል።
- ነወዊይ እንዲህ ብለዋል: "ዑለማዎች (ሽርጣቸውን ያጠብቁ ነበር) በሚለው ትርጉም ዙሪያ የተለያየ ሃሳብ አላቸው። ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከሌላው ጊዜ በተለየ ልምዳቸው ጨምረው በማምለክ መታገላቸውን ለመግለፅ ነው፤ ያሉም አሉ። ትርጉሙ ለአምልኮ መታጠቃቸው ነው። "ለዚህ ጉዳይ ሽርጤን አጠበቅኩኝ።" ሲባል ለርሱ ታጠቅኩኝ ተዘጋጀሁ ማለት ነው፤ ያሉም አሉ። በአምልኮ ለመጠመድ ሴቶችን መራቃቸውን ለመግለፅ የተጠቀሙት ቃል ነውም ተብሏል።