- መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ ለሴቶች እንኳን ሳይቀር የሸሪዓ ደንቦችን ካሟላች የተደነገገ ጉዳይ ነው። ይህ ግን ፈተና የማይገጥም ከሆነ ነው።
- በረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናት ላይ ኢዕቲካፍ ማድረግ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አዘውትረው ስለሰሩት አፅንኦት የተሰጠው አምልኮ ነው።
- ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በኋላ ሚስቶቻቸው ኢዕቲካፍ ስላደረጉ ኢዕቲካፍ ያልተሻረ ቀጣይነት ያለው ሱንና መሆኑን እንረዳለን።