- ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙ ትክክለኛ መሆኑን እንረዳለን።
- ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው በምርጫው ስላልሆነ መብላቱ ጥፋተኛ አያደርገውም።
- አላህ ለባሮቹ ያለውን እዝነትና ለነረሱ ማቅለሉን፣ ጭንቅና ችግርንም ከነርሱ ላይ ማንሳቱን ተረድተናል።
- አንድ ጾመኛ ሶስት መስፈርቶች የተሟሉ ጊዜ ካልሆነ በቀር ጾሙን አይፈታም። አንደኛ: አውቆ መሆኑ ነው፤ የማያውቅ ከሆነ አይፈታም። ሁለተኛ: እያስታወሰ መሆን አለበት። ረስቶ ከሆነ የበላው ጾሙም ትክክለኛ ነው። (ሲያስታውስ እስከታቀበ ድረስ) በርሱም ላይ ምንም ቀዿእ አይኖርበትም። ሶስተኛ: ፈቅዶ መሆን አለበት። ተገዶ መሆን የለበትም። በምርጫው የሚያስፈታ ነገር መውሰድ አለበት።