- የረመዷን ወር ደረጃን እንረዳለን
- ይህ የተከበረ ወር የአምልኮና የመልካም ተግባር ወቅት ከመሆኑ አኳያ ይህ ሐዲሥ ለጾመኞች ብስራት ነው።
- ረመዷን ውስጥ ሸይጣኖች መጠፍነጋቸው የትኛውም ለአቅመ አዳም የደረሰ ሰው ወንጀል ለመስራት ምክንያት እንደሌለው ለመጠቆም ነው። "ሸይጣኖች ወደ አንተ እንዳይቀርቡ ስለተጠበቅክ አምልኮ ለመተውህና ወንጀልን ለመስራትህ እነርሱን ምክንያት እንዳታደርግ።" የተባለ ነው የሚመስለው።
- ቁርጡቢይ እንዲህ ብለዋል: «"በረመዳን ውስጥ ብዙ ክፋትና ወንጀሎች ሲከሰት እንዴት እናያለን? ሸይጣኖች ቢታሰሩ ኖሮ ይህ አይከሰትም ነበር።" ቢባል። መልሱ: ክፋቶችና ወንጀሎች የሚያንሱት መስፈርቶቹን የጠበቀና ስነስርዓቱን ያሟላን ጾም ከጾሙ ሰዎች ላይ ነው። ወይም የሚታሰሩት በአንዳንድ ዘገባዎች ቀደም ተብሎ እንደተጠቀሰው ሁሉም ሳይሆኑ አመፀኛ የሆኑት የተወሰኑ ሸይጣኖች ብቻ ናቸው። ወይም በሐዲሡ የተፈለገው ክፋቶች እንደሚያንሱ መጥቀስ ነው። ይህም ደግሞ በገሃድ የሚታይ ነገር ነው። ከሌላ ጊዜ በተለየ ወንጀሎች በረመዷን መከሰታቸው እጅግ የመነመነ ነውና። በተጨማሪም ሁሉም ሸይጣኖች በመታሰራቸው ክፋትና ወንጀል አይከሰትም የሚለውን አያሲዝም። ወንጀል ለመስራት እንደ ቆሸሸች ነፍስ፣ መጥፎ ልምዶችና የሰው ሸይጣኖችን የመሰሉ ከጂን ሸይጣን ውጪ ያሉ ሌሎች ምክንያቶችም ስላሉ።