/ (ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።

(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸው - እንዳስተላለፉት እንዲህ ብለዋል፦ የአላህ መልዕክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦ "(ግዴታነቱን) አምኖ እና ምንዳውን ከአላህ አስቦ የረመዳንን ወር የፆመ ሰው ያለፈ ወንጀሉ ይማርለታል።"
ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን የረመዳንን ወር በአላህ አምኖ፣ በፆም ግዴታነትና አላህ ለፆመኞች ያዘጋጀውን የደለበ ምንዳና አጅር እውነት ብሎ እንዲሁም ፆሙም ለይዩልኝና ይስሙልኝ ሳይሆን የአላህን ፊት ፈልጎበት የፆመ ሰው ያለፈው ወንጀሉን እንደሚማር ነገሩን።

Hadeeth benefits

  1. በረመዳን ፆምም ይሁን በሌሎች መልካም ስራዎች ላይ ኢኽላስ ያለውን ትሩፋትና አንገብጋቢነትን እንረዳለን።